ንጹህ አየር
ንጹህ ውሃ
ደህንነቱ የተጠበቀ ምግብ
ጥሩ ጤና
...for a BetterLife™

የምንሰራቸው ስራዎች

ውሃ

አየር

ምግብ

ጤና

ስለ ኩባንያችን

ነገሮችን ለህይወት ተስማሚ እንዲሆኑ የሚያደርጓቸው ብዙ ገጽታዎች አሉ። ኩባንያችን አጽንኦት የሚሰጥባቸው ቁልፍ ነገሮች ንጹህ አየር፣ ንጹህ ውሃ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ ምግብ እና ጥሩ ጤና ናቸው።

የአካባቢ ጽዳትና ንፅህና አጠባበቅ አንገብጋቢ በሆነባቸው የዓለም ክፍሎች ውስጥ፣ እያደገ የሚሄድ የተሻለ የኑሮ ደረጃ የመኖር ፍላጎት አለ። Good for Life (ጉድ ፎር ላይፍ) የእነዚህን ማህበረሰቦች ሁኔታ ለማሻሻል እና በእነዚህ ማህበረሰቦች ውስጥ የሚኖሩ ሰዎችን ህይወት ለማሳደግ የሚያስችሉ መፍትሄዎችን ይሰጣል። እነዚህ ሰዎች የተሻለ ንጽህና ያለው የመጠጥ ውሃ፣ ይበልጥ ተደራሽነት ያለው ውሃ፣ በቤት ውስጥ ንጹህ አየር፣ ደህንነቱ የተጠበቀ የምግብ ዝግጅት እና አጠቃላይ ጤና እና ደህንነትን የማግኘት እድሉ ይኖራቸዋል።

ከGood for Life (ጉድ ፎር ላይፍ) ጋር ከእንግዲህ ልጆቻችን በተመሰቃቀለ እና ዘላቂነት በሌለው ዓለም ውስጥ ያድጋሉ ብሎ መፍራት አያስፈልግም። ለእርስዎ፣ ለማህበረሰብዎ እና በአጠቃላይ ለህይወት መልካም ከሆኑ ነገሮች ጋር በተያያዘ ያለማቋረጥ ምርቶቻችን በማምረት ላይ እንገኛለን። Good for Life (ጉድ ፎር ላይፍ) በጣም ዘመናዊው የሆነ ንጹህ ቴክኖሎጂን ለዓለም እያቀረበ ያለ የአውስትራሊያ ኩባንያ ነው። ኩባንያችን የተመሰረተው ሌሎች ሰዎች የተሻለ እና ንፁህ ኑሮ እንዲኖራቸው ለማስቻል የጋራ ፍላጎት ባላቸው በጥቂት አውስትራሊያዊ ስራ ፈጣሪዎች ነው።

እነዚህ ባለሙያዎች የተለያየ የትምህርት እና የስራ ልምድ በሚከተሉት ዘርፎች ይዘዋል፥ በአስተዳደር፣ በምህንድስና፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በግብይት፣ ዘላቂነትን በማማከር እና ታዳሽ ኃይል። በየተሰማሩባቸው የስራ መስኮች ላይ የብዙ አመታት ልምድ ያላቸው መሆኑ የሰው ልጆች ደህንነት እና አካባቢያቸው ሁልጊዜም ቅድሚያ ሊሰጣቸው እንደሚገባ ለመገንዘብ አስተዋፅኦ አድርጎላቸዋል።

ጠንክሮ ከመስራት እና በጽናት ከመታገል ብዛት ለ'እኔ' መልካም የሆነ ነገር ለ'እኛ' መልካም የሆነ ነገር መሆኑን ለመረዳት ችለዋል፣ ያም ማለት በንድፍ ደግሞ Good for Life (ጉድ ፎር ላይፍ) ማለት ነው።

የቡድናችን አባላት

Adam Elson አዳም ኤልሰን

የኩባንያው ዳይሬክተር
ንጹህ ውሃ እና አየር የአዳም ከፍተኛ የፍላጎት መስኮች ሲሆኑ የሰዎችን ህይወት የተሻለ ለማድረግ በእስያ እና በተቀረውም የዓለም ክፍል ለእነዚህ ጉዳዮች መፍትሄ መስጠት ግንባር ቀደም አላማው ነው። አዳም በእስያ ውስጥ ከ 12 ዓመታት በላይ ሲሠራ ቆይቷል። የትውልድ ቦታው አዴላይድ ሲሆን፣ በቤይጂንግ ውስጥ በኑሮ እና ስራ ዓለም ቆይቷል፤ በአሁኑ ጊዜ ታይዋን ውስጥ ይኖራል።

Andrew Cromarty አንድሪው ክሮማርቲይ

የምህንድስና ዳይሬክተር
አንድሪው በውሃ ማቀነባበር፣ በታዳሽ ኃይል እና የውሃ እንቅስቃሴ መስኮች ዙሪያ በአሁኑ ሰዓት ያሉትን እና አዳዲስ ቴክኖሎጅዎችን በማጣመር የምህንድስና መፍትሄዎች መፍጠር ትልቁ ህልሙ ነው። አንድሪው በባንክ፣ በምህንድስና እና በማኑፋክቸሪንግ መስኮች በበርካታ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ውስጥ የስራ አስፈፃሚ ሚናዎች ላይ ልምድ ያለው በመሆኑ፣ የንግድ ግንዛቤን፣ ስልቶችን ማጎልበት እና የምርት ልማትና ፈጠራን ለቡድኑ ያበረክታል።

አበበ ጌታቸው

የንግድ ልማት ሥራ አስኪያጅ
አበበ ከፍተኛ ተነሳችነት ያለው ኢትዮጵያዊ ሲሆን ሃገሩን በጣም የሚወድ እና ኢትዮጵያን የተሻለች ለማድረግ ሳይታክት የሚሰራ ነው። በታዳሽ ኃይሎች ዙሪያ ከፍተኛ ፍላጎት ያለው ሲሆን፣ በቅርቡ ሁሉም ተጠቃሚ የሚሆኑባት እራሷን የቻለች፣ ዘላቂነት ያላት ኢትዮጵያን ማየትን አላማው አድርጎ መስራት ይፈልጋል።

Mulatu Tafesse

Ethiopia Director

ውስን ጉዳይ ተኮር ጥናቶች

ዛሬውኑ ያነጋግሩን